Harari Attorney General

Government of Harari People Regional State

በምግብ ዉስጥ መርዝ በመጨመር የግድያ ወንጀል የፈፀመችዉ ወጣት በእስራት ተቀጣች***

February 11, 2026
4:55 PM
0 views
ተከሳሽ ሱመያ ሙሳ አብራሂም የተባለችዉ የ15 አመት ወጣት በሀረሪ ክልል ድዬ ጠያራ ወረዳ ሚያይ ቀ/ገ/ማህበር ገንደ አመድ በሚባል ስፍራ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 7:00 ሰአት ተከሳሽ የሆነዉ ይሁን የሚመጣዉን ዉጤት ለመቀበል አስቀድማ በማሰብ ለተበዳዮቹ ባዘጋጀችዉ የሳህን ምግብ ዉስጥ መርዝ በመጨመር ታጁ አሊ የተባለዉ ምግቡን ሲመገብ በመመረዙ ሂወቱ ሲያልፍ ሌላኛዉ የግል ተበዳይ ፌሮምሳ ሸሪፍ ምግቡን ተመግቦ ቢመረዝም ህክምና ተደርጎለት የተረፈ በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመችዉ ሰዉ የመግደል ወንጀል በሁለት ተደራራቢ ክስ ተከሳለች።
ተከሳሽ በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 58(1)(ለ) እና 540 እና በተመሳሳይ በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 27(1)58(1)(ለ)እና 540 ላይ የተደነገገዉን በመተላለፍ ተከሳለች::
ጉዳዩን የያዘዉ የሀረሪ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳሬክቶሬት አቃቢ ህግ የተፈፀመዉን ወንጀል በሰዉናበሰነድ ማስረጃ ካጠናከረ በኃላ ለክልሉ ከፍተኛ ፍ/ ቤት ጉዳዩን ያስረዳ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ዛሬ 21/5/2018ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ በ17 አመት እስራት እንድትቀጣ ወስኗል።